ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን እስከ ሞት የሚያስቀጣ የህግ ማዕቀፍ እየተጠናቀቀ ነው
*****************************************************
*****************************************************
ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የድንበር ማሻገርና በሰው መነገድ ወንጀሎችን መቆጣጠር ያስችላል የተባለውና እስከሞት የሚያስቀጣ አንቀጾችን ያካተተ ጠንከር ያለ የህግ ማዕቀፍ እየተጠናቀቀ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡
በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱሉ እንደተናገሩት በርካታ አምራች ወጣቶች በደላሎችና በህገ ወጥ ድንበር አሻጋሪዎች ለእንግልት፣ ለስቃይ እንዲሁም ለሞት እየተዳረጉ በመሆኑ ወንጀሉን ለመቆጣጠር የሚያስችል ጠንካር ያለ የህግ ማዕቀፍ አስፈልጓል፡፡
በወንጀል
ድርጊቱ በርካታ ወጣቶች የአካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና አልፎም የህይወት መጥፋት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡
በሀገራቸው
መስራትና ማምረት የሚችሉ በርካታ ወጣቶች በደላሎችና ህገ ወጥ ድንበር አሻጋሪዎች ተጠቂ በመሆናቸው ለጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑም አክለዋል፡፡
ረቂቅ
አዋጁ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተገቢ ቅጣት እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ረቂቅ
አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ለህግና ፍትህ ዴሞክራሲያዊ ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም ለሴቶች፣ወጣቶችናማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ ቀርቧል ተብሏል፡፡
ጉዳዩ
አስከፊና አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ ከሚቀርቡትና ቶሎ ከሚጸድቁት የህግ ማዕቀፎች ውስጥ ቅድሚያ እንዲያገኝ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ወንጀሉ
በሃገር ውስጥና በውጭ ሃይሎች በቅንጅት የሚሰራ በመሆኑ ችግሩን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ድንበር አካባቢ ካሉ ጎረቤት አገራት ጋር በቅንጅትና በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ እንደተደረሰ አቶ ዝናቡ ገልጸዋል፡፡
ችግሩንም
በዘላቂነትለመፍታት የህግ ማዕቀፎች ማዘጋጀቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ህብረተሰቡ ላይ ለውጥ ማምጣጥት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ላይ እና የስራ አድል ፈጠራ ላይ በስፋት መስራት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
ወጣቱ
በሃገሩ ሰርቶ የሚለወጥበት፣ሃብት ንብረት የሚያፈራበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በዚህ
ወንጀል ድርጊት የሚሳተፉ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ከጸጥታ ሃይሉ ጎን ለጎን የህብረትሰቡ ትብብር፣ የወንጀሉ ተጎጅ አካላት ተባባሪ መሆን ወሳኝ ነውም ነው የተባለው፡፡

No comments:
Post a Comment